ሕወሓት የ47 ዓመት የጎሠኝነት እድፍ ነው። ይህ እድፍ ለማጽዳት በደንብ ማሸት ያስፈልጋል።

 

ጎሠኞች የኢትዮጵያን ታሪክ ሳያውቁ ቀርተው ወይም ማወቅ ተስኗቸው አይደለም። ሠው መሆን አቅቷቸው ነው ሠው መሆን የትግሉ ሜዳ ይሠፋባቸዋል።ጎሰኝነት የከፈ አስተሣሠብ መሆኑ ግልጽ ነው፣ በማሕበራዊ ፍልስፍና ጎሠኝነት ኃላ ቀርና በታኝ በሽታ ነው። ጎሠኞች ''ዘመድ ከዘመዱ አህያ ከአመዱ'' የሚል ብሂል አላቸው። ክልሎች የወያኔ አገዛዝ ውላጆች ናቸው ሆን ተብሎና ታስቦበት የኢትዮጵያን ሕዝብ በጎሣ ከፋፍሎ በፋክክር በማፋጠጥ የበላይነትን ይዞ ለመቆየት የታሠበ የትንንሽ ልጆች ቅዠት ነው።ወያኔ ክልሎችን አካለ ስንኩላን አድርጎ የፈጠረው ለብልሀቱ ነው።ዋናው አላማ ጎሣዎችን በማናከስ ዳኛ ሆኖ አናታቸው ላይ ለመቀመጥ ነበር።

ይህን መጽሐፍ አንብበ ስትጨርስ ‹‹ለወያኔ ዘጠኝ ሞት ይገባዋል!›› ትላለህ፡፡

  ‹‹የታፋኙ ማስታወሻ›› አንብበ ስትጨርስ ይህን ሁሉ ግፍ የፈጸሙ ሰው መሳይ አውሬዎች ከድል ማግስት አስከሬናቸው ከነስም አጠራራቸው እንዲጠፋ እንደ ጋዳፊ የሰሐራ በርሃ ላይ እንዲቀበር ወይም እንደ ኦሳማ ቢን-ላደን ሜዲትራንያን ላይ እንዲሰጥም ትመኛለህ። አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ እጅ የደረሰበት አፈና -ሰብአዊ ተግባር ሲገልጽ ምን አይነት እርኩስ መንፈስ ያደረባቸው ሰዎች አገሪቱና ሕዝቧ ለሦስት አስርት ዓመታት እንደተመሩ ስታውቅ እጅጉን ታዝናለህ፡፡ 4 ዓመታት [2006-2010] በአንዳርጋቸው ላይ ያደረሱበትን መከራ 308 ገጽ 4 ክፍል ተሰንዶ በሕይወት ላለነው ለቀጣይ ትውልድ ምን አይነት ስርዓት ኢትዮጵያ ውስጥ እንደነበርና ዳግም ይህን የመሰለ ክፉ መንፈስ የተጣባው ሥርዓተ-መንግሥት በአገራችን ላይ እንዳይከሰት መማሪያ ይሆን ዘንድ በመጽሐፍ መልክ አቅርቦልናል፡፡ የመጽሐፉ መታሰቢያነት ‹‹ግፈኛውን የወያኔ ስርአት ለማስወገድ ህይወታቸውን ከመስጠት አንስቶ ሌሎችንም መስዋዕትነቶችን ለከፈሉ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች›› ይሁን ብሏል፡፡

ZERO TOLERANCE , DISMANTLE AND REMOVE


ይህ የዘመናችን ጋንግሪኑ መቆረጥ አለበት! ውጊያው ከገሐነም ካመለጠ አጋንንት ጋር መሆኑ ጀነራሉ ነግረውናል በሁለተኛው የዓለም ጦርነት መጨረሻ ላይ የጀርመን ናዚ ጦር አባላት በሽሽት ላይ እያሉ ያገኙትን ጀርመናዊ ያልሆነ ፍጡር በመጨፍጨፍ ንዴታቸውን ይወጡ ነበር። የወያኔ ልዪ ኃይል እና ሚልሻ የፈጸመው ብሄር ተኮር የጅምላ ፍጅት የሂትለር ወታደሮችን ድርጊት ዳግም እንድናስታውስ ያደርገናል። ሕዋሓት ንጹሀንን በጨፈጨፈች ቁጥር ድሉን የበለጠ ታቀርበዋለች።#ማይካድራ የንፁሃን ዜጎች ደም የሚጮህባት፣ በታሪክ ሰንሰለት ቁስልና ህመሙ የማይሽርባት የደም ምድር ሆና ትቀጥላለች።


ምክር ቤቱ የዶ/ር ደብረጸዮን ገብረሚካኤልን ጨምሮ የሌሎችን ግለሰቦች ያለመከሰስ መብት አነሳ

 #Ethiopia : የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተለያዩ ወንጀሎች የጠረጠራቸውን ግለሰቦች ያለመከሰስ መብታቸው እንዲነሳ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አፀደቀ።

በዚህም መሰረት፦

1.     ዶክተር ደብረጸዮን ገብረሚካኤል

2.     አቶ አስመላሽ ወልደሰንብት

3.     አቶ አባይ ፀሃዬ

4.     ዶክተር አምባሳደር አዲስ ዓለም ቤሌማ

5.     አቶ ጌታቸው ረዳ

6.     አቶ አፅበሃ አረጋዊ

አቶ ገብር እግዚአብሄር አርአያ እና ሌሎችም ላይ የቀረበው ያለመከሰስ መብት የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ ፀድቋል።

ግለሰቦቹ የተጠረጠሩበት ወንጀሎችም ጦር መሳሪያ ይዞ በማመፅ፣ የሀገር መከላከያን በመውጋት እና በሌሎችም ተያያዥ ወንጀሎች ዋና አድራጊነት ነው መሆኑ ታውቋል።

 


New Post

 Abebeb